ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ነባር እና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

ማስታወቂያ

ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ

ነባር እና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

 

የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛው የቅድመ ምረቃ መርሀ ግብር

 • የነባር ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 21 እና 22 ቀን 2012 ዓ.ም
 • የነባር እና አዲስ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሁም
 • የአዲስ ገቢ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 27 እና 28 ቀን 2012 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

 

ስለሆነም ነባርና አዲስ ተማሪዎች በተገለጸው ፕሮግራም መሰረት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን፤ አዲስ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ

 • ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
 • የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት
 • የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ካርድ ኦሪጅናል እና ኮፒ
 • 3×4 የሆነ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ እንዲሁም
 • ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እናሳውቃለን፡፡

በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ከአዲስ አበባ የአውቶቢስ መናኻሪያዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቸን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

 • በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የሐላፊነት መውሰጃ ፎርም ካላችሁበት ወረዳ አስፈርማችሁ ማምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
 • ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 • የተከታታይ ትምህርት መርሀ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ በዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ ይገለጻል፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቀጥር ፡- ( 0118959462/63 ይደውሉ ወይም የዩኒቨርስቲውን ድረ ገጽ aastu.edu.et ይጎብኙ፡፡

 

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ  

                     ሬጅስትራር ጽ/ቤት

 

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *