ማስታወቂያ ለተከታታይ ትምህርት ፈላጊዎች

ማስታወቂያ ለተከታታይ ትምህርት ፈላጊዎች

የአዲስ አበባ ሣይንስና ቱክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 ዓ.ም በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ ከታች በተዘረዘሩት በቂ ተመዝጋቢ በሚገኝባቸው ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞች

 • Civil Engineering
 • Software Engineering
 • Mechanical Engineering
 • Electro-Mechanical Engineering
 • Electrical Engineering
 • Construction Technology & Management

የመግቢያ መስፈርቶች

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ባወጣው መስፈርት መሰረት ሲሆን

እነዚህም፡-

 1. የመሰናዶ ትምህርት አጠናቀው የዓመቱን የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ያላቸው ወይም
 2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማዕቀፍ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመሸጋገሪያ መመሪያ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟሉትን

ሀ. የ10ኛ ክፍል ወይም የቀድሞ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ

ለ. የደረጃ አራት የብቃት ምዝና (COC level 4) ወስደው ያለፉ

ሐ. በሰለጠኑበት ሙያ ቢያንስ የአንድ ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው እና

መ. ተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ያለፉትን/እንዲሁም

 1. ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤

የማመልከቻ ቦታ

ሬጅስትራር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክሎጂ ዩኒቨርስቲ

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ (ቂሊንጦ)

የማመልከቻ ጊዜ

ከነሐሴ 20-30/12/2011 ዓ.ም

የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

 • የትምህርት ማስረጃ ኦሪጂናል እና ፎቶ ኮፒውን
 • አራት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
 • የማመልከቻ ክፍያ 100 ብር በዩኒቨርስቲው የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ በ አካውንት ቁጥር 1000007971544 የተከፈለበት የባንክ ስሊፕ ያቀርባሉ፡፡
 • በ 2011 ዓ.ም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ የመሰናዶ ተማሪዎች በስተቀር ማንኛውንም አመልካች ከወጪ መጋራት ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተመደቡበት/ከተመረቁበት ተቋም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ

 • የመጀመሪያ ድግሪ (Extension) ፕሮግራሞች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ ቡልቡላ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት (ሳሪስ) ሲሆን በቅዳሜና ዕሁድ የመጀመሪያ ፕሮግራም እና የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው በዋናው ዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
 • በተጨማሪም በዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ aastu.edu.et በማስታወቂያ የሚገለጽ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *