የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጡ

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጡ

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መስከረም 9፣2012 ዓ.ም በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች በሚገኙ 40 የመፈተኛ ጣቢያዎች መግቢያ ፈተና ሰጡ፡፡

ፈተናዉን የወሰዱ ከ2100 በላይ ተማሪዎች በአዲስ አበባ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው መርሃ ግብር በሚሰጡ የኢንጅነሪንግ እና የአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸዉን  ለመከታተል ፍላጎት ያላቸው ሲሆኑ የመግቢያ ፈተናዉ የባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እውቀታቸውን መሰረትያደረገ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡በመጨረሻም በሁሉም የመፈተኛ ጠቢያዎች ሲካሄድ የነበረዉ  ፈተና በሰላም ተጠናቋል፡፡

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *