የ አ.አ.ሣ.ቴ.ዩ. 10ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

ጥቅምት 6/2010ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ 10ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በአገር አቀፍ ደረጃ “ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ግብ ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል ለ10ኛ ጊዜ የተከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ፡፡

እለቱን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኑርልኝ ተፈራ በተወካያቸው   የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የቴ/ሽ/ም/ፕሬዘዳንት በሆኑት ዶ/ር አዳነ አብርሃም  እንደተናገሩት “ አያት ቅድመ አያቶቻችን ለሰንደቅ ዓላማችን ሲሉ ክቡር  ሕይወታቸውን እንደከፈሉ ሁሉ ወጣቱም የማንነቱ መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡”

አያይዘውም ተቋማችን የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚያከብረው በሀገራችን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈን ከመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ  ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመቀበል እንዲሁም ዩኒቨርስቲውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የሚረዱንን ብቁ መምህራን ፣ በአግባቡ የተደራጁና የተሟሉ ላቦራቶሪዎች ለማዘጋጀት እየሰራን ባለንበት ወቅት ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ብላ የምትውለበለበውና የምንከበርባት ድህነትን ፤ ጠባብነትንና ትምክህተኝነትን በማጥፋት መሆን እንደሚገባው የተናገሩት ተወካዩ ዶ/ር አዳነ የኢትዮጵያ ሠንድቅ ዓላማ በክብር እንዲውለበለብ ክቡር ህይወታቸውን የሰውትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፣መሰዋትነት፣እያስታወስን የሠንደቅ ዓላማ ቀንን እናከብር ዘንድ  ጥሪየን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ ተወካዩም በንግግራቸው መጨረሻም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል በልማት የበለፀገች ኢትዮጵያን ስንገነባ በመሆኑ፣ በየስራ መስካችን ተግተን ልንስራ  ይገባል ብለዋል፡፡

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *