.የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ንጽህና መጠበቅያ ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲየአለም የጤና  ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የእጅ ንጽህና መጠበቅያ ሳኒታይዘር ማዘጋጀት ጀመረ፡
የኮሮና ቫይረስን ለማከላከል በምደረገው ጥንቃቄ እጅን በአግባቡ በውሃና በሳሙና መታጠብ አልያም በሳኒታይዘር ማጽዳት አንዱ መንገድ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ የተነሳ በሳኒታይዘር አቅርቦት እና ፍላጎት ላይ ክፍተት ይታያል፡፡ ይህንን ክፍተት በማየት የዩኒቨርሲቲያችን የኬሚካል ምህድስና ትምህርት ክፍል (Chemical Engineering Department) ሳንታይዘር (Hand Sanitizer) ማዘጋጀት የጀመረ ሲሆን፤ቀደም ብሎ በሙከራ ደረጃ ለተወሰኑ የስራ ክፍሎች ስሰጥ የነበረው፤ ከትላንትና /16/07/2012ዓ.ም/ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲው ማህብረሰብ በሙሉ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን ከቫይረሱ እንዲከላከል በነፃ እየታደለ ይገኛል፡፡

ከዝህ በተጨማሪን ዩኒቨርሲቲው  እያተዘጋጀ ከለው 250ml ሳኒታይዘር 500pc በክፍለ ከተማው ለሚኖሩ የመግዛት አቅም ለሌላችው የማህብረሰብ ክፍል እንዲደርስ ዛሬ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ት/ም ሚንስተር ዴኤታ ለክ/ከተማው ስራ አስፈጻሚ አስረክቧል፡፡ በእርክብክቡ ወቅትም ዶ/ር ሳሙኤል የአዲስ አበባ ሳንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአከባቢውን ማህብረሰብ ችግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በማድነቅ መሰል ተግባራት በከፍተኛ ት/ም ተቋማት ተጠናክረው መቀጠል እደለባቸው እና የመንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በተለያዩ የማህብረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላይ ሲሳተፍ መቅየቱን ያስተወሱት የክ/ከተማው ስራ አስፈጻሚ፤ በአሁኑ ወቅት በሳንታይዘር አቅርቦት ላይ ያለውን ክፍተት በመለየት በተለይም በራሱ ቤተሙከራና በራሱ አቅም በማዘጋጀት ለበረከተው ልገሳ አመስግነዋል፡፡ የማህብረሰቡን ችግር በመለየት ችግር ፈቺ የሆኑ መሰል የምርምር እና የፈጠራ ተግባራት በተቋሞቻችን ተጠናክራው መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለማከላከል መንግስት እያደረገ ያለውን ግብግብ ለማገዝ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይም በሚቻለው አቅም ሁሉ የራሱን አስተዋዕፆ እደሚያበረክት የገለጹት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት፤ ሁሉም ማህብረሰብ በያለበት መንግስት የሚሰተውን አቅጣጫ በመከተል ለራሱንና በአከባቢው ለላው ህዝብ ተገቢውን ጥንቃቄ በማደረግ ቨይረሱን እንድንከላከል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *