የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ብራና የባህልና የኪነጥበብ ማዕከል ቡድን በመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ያሉ ወገኖቻችንን ጎበኙ፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ብራና የባህልና የኪነጥበብ ማዕከል ቡድን በመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ያሉ ወገኖቻችንን ጎበኙ፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የብራና የባህልና የኪነጥበብ ማዕከል አመርቂ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የኪነጥበብማዕከሉ በተማሪዎች አገልግሎት ዳሬክቶሬት ስር በሚገኘዉ ስፖርትና ክለባት ቢሮ ስር የሚገኝ በተማሪዎች የቋቋመ ማዕከል ሲሆን በዉስጡ አንድ መቶ አርባና አንድ(141 ) አባላትና አምስት(5) ክፈሎችአሉት፡፡እነሱም የስነፅሁፍ ክፍል፤የቴያር ክፍል፤ የሙዚቃ ክፍል፤የስዕልና ቅርጸቅርፅ ክፍል እና የዉዝዋዜክፍል ናቸዉ፡፡ማዕከሉ የተለያዩ የመዝናኛ ፐሮግራሞችን በማቅረብ የዩንቨርሰተቲዉን ማህበረሰብ እያዝናና ቁምነገሮችን በማስጨበጥ፤የበዓላት ቀኖችን በማድመቅ፤የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም አስተማሪና አዝናኝ ፐሮግራሞችን በማዘጋጀትና በማቅረብ ጉልህ ሚና ያጫወታል፡፡በ2012 የትምህርት ዘመን የመጀመሪ መንፈቅ አመትም በጥቅምት ወር ለተማሪዎች እንኳን ደህና መጣቹህ፤ህዳር 16 የቴያትር ምሽት፤ህዳር 25 የሙዚቃ ምሽትእና የስነፅሁፍ ምሽቶችን ያቀረበ ሲሆን በዩንቨርሲቲዉ የተከበሩ የኤችአይቪ ኤዲስ ፤የፀረ ሙስና ቀናት ላይ በመገኘት ዝግጅታቸዉን ቀረቡ ሲሆን በታህሳስ 12 በሜቄዶንያ የአረጋያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ታላቅ ፐሮግራም በማቅረብ ማህብረሰቡን ለማገልገል ያለውን አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *