ማስታወቂያ—– ለተከታታይ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

 

የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ2011 ዓ.ም በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በቅዳሜ እና እሑድ በመጀመሪያ በሁለተኛ ድግሪ በቂ ተመዝጋቢ በሚገኝባቸዉ  ከታች በተዘረዘሩት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

 

በመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞች

 

 • Civil Engineering
 • Construction Technology & Management
 • Electrical Engineering
 • Software Engineering
 • Mechanical Engineering
 • Electro-Mechanical Engineering

በሁለተኛ ዲግሪ (በእረፍት ቀናት የሚሰጥ)

 

 • Sc. Degree in Mechanical Engineering (Manufacturing Engineering )
 • Sc. Degree in Mechanical Engineering (Thermal Engineering)
 • Sc. Degree in Electrical and Computer Engineering (Power System Engineering)
 • Sc. Degree in Electrical and Computer Engineering (Communication Engineering)
 • Sc. Degree in Electrical and Computer Engineering (Computer Engineering)
 • Sc. Degree in Software Engineering
 • MBA Degree in Construction Management
 • MBA Degree in Industrial Management

 

 

የመግቢያ መስፈርቶች

 

ለመጀመሪያ ድግሪ

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ባወጣዉ መስፈርት መሰረት ሲሆን እነዚህም፡-

 

 1. የመሰናዶ ትምህርት አጠናቀዉ የዓመቱን የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ት/ት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ያላቸው ወይም
 2. የቀድሞ 12ኛ ክፍል ወይም የአሁኑ 10ኛ ክፍል አጠናቀዉ ደረጃ 4 የቴክኒክና ሙያ ት/ት ያጠናቀቁ እና የ COC  ፈተና ያለፉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ና ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና የሚያልፉ ወይም
 1. ከታወቀ ከፍተኛ የት/ት ተቋም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸዉ፤

ለሁለተኛ ዲግሪ

 • በተዛማጅ የትምህረት መስክ ከታወቀ ተቋም የተመረቀ/ች፡፡
 • አጠቃላይ አማካኝ ለሴት በ 2.5 እና ለወንድ 2.75 ነጥብ በላይ ያለው/ላት፡፡

 

የማመልከቻ ቦታ

አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ሬጅስትራር ጽ/ቤት

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ (ቂሊንጦ)

 

የማመልከቻ ጊዜ

ከነሐሴ 17 እስከ ጳጉሜ 02/2010ዓ.ም በመደበኛ የሥራ ሰዓት ብቻ

 

 

 

የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

 • የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ
 • ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድፎቶግራፍ
 • የማመልከቻ ክፍያ 100 ብር በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ Acc. No፡ 1000007971544 የተከፈለበት የባንክ ደረኝ በአካል ይዞ መቅረብ፡፡

 

 

 

ማሳሰቢያ

 

 • የመጀመሪያ ድግሪ(Extension) ፕሮግራሞች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ ቡልቡላ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት (ሳሪስ) ሲሆን በቅዳሜና እሑድ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ፕሮግራሞች ደግሞ በዋናው ዩኒቨርሲቲ ጊቢ  ውስጥ ይሆናል፡፡
 • የመግቢያ ፈተና የሚያስፈልጋቸዉ እጩዎች/ፕሮግራሞች በቡልቡላ ከፍተኛ መሰናዶ ት/ቤት(ሳሪስ) እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ሲሆን ማን የት እነደሚፈተን በዩኒቨርሲቲዉ  ድረ ገጽ aastu.edu.et  እና በማስታወቂያ የሚገለፅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

 

 

ለበለጠ መረጃ  011-812-42-08 ወይም 011-895-94-63  ይደውሉ፡፡