የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት አመራር ስርዓት ISO 9001:2015 QMS ትግበራን በተመለከተ ስልጠና ሰጠ
ታህሳስ 10 ቀን 2016
****************
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የጥራት ማበልጸጊያ ዳይሬክቶሬት የጥራት አሰራር ስርዓት QMS ISO 9001:2015 ትግበራን በተመለከተ ለዲኖት፤ ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና አካዳሚክ ዘረፉ ዳይሬክተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል ኢብራሂም እንደገለጹት ስራዎችን በወጥነትና በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ ለመከወን እንዲንሁም የISO ሰርቲፍኬት ለማግኘት ላለፉት ሁለት ዓመታት በየደረጃው ስራዎች እየተሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም የአካዳሚክ ዘርፉ ስራውን የራስ በማድርግ ወደ ትግበራ እንዲገባ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ከስልጠናው በኃላ በአካዳሚክ ዘርፉ ያሉ የአሰራር ስርዓት ሰነዶች በሙሉ ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ መጽደቅ እንደሚጠበቅባቸው የገለጹት ዶ/ር ከማል በተቋም ደረጃ ከ3ኛ ሩብ ዓመት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የISO ትግበራ አቅጣጫ የተቀመጠ በመሆኑ ከስልጠናው የተገኘውን ግንዛቤ በየስራ ክፍሉ ላሉ ባለሞያዎች/ፈጻሚዎች ተገቢው ግንዛቤ ማስጨበጥና አፈጻጸሙን መከታተል ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የግንዛቤ ስልጠናው በISO መሰረታዊ እሳቤዎችና አስፈላጊነት እንዲሁም በዝግጅትና በትግበራ ወቅት ልንከተላቸው የሚገቡን መሰራታዊ ዝርዝሮች ያካተተ ሲሆን፤ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ከአሰልጣኞች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
Fusce dapibus, tellus ac cursus commodo, tortor mauris condimentum nibh, ut fermentum massa justo sit amet risus. Maecenas faucibus mollis interdum. Vivamus sagittis lacus vel augue laoreet rutrum faucibus dolor auctor. Aenean eu leo quam. Pellentesque ornare sem lacinia quam venenatis vestibulum. Sed posuere consectetur est at lobortis.
Duis mollis, est non commodo luctus, nisi erat porttitor ligula, eget lacinia odio sem nec elit. Aenean eu leo quam. Pellentesque ornare sem lacinia quam venenatis vestibulum. Vivamus sagittis lacus vel augue laoreet rutrum faucibus dolor auctor. Donec id elit non mi porta gravida at eget metus.
Nullam id dolor id nibh ultricies vehicula ut id elit. Donec ullamcorper nulla non metus auctor fringilla. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Cras mattis consectetur purus sit amet fermentum.