ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ገለፃ አደረገ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም 1574 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡ በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዜሮ ዋን ዜሮ ዋን አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ለተማሪዎች የቅድመ-ግንዛቤ ገለፃ (Orientation) ሰጥተዋል፡፡ በገለፃ መርሃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ ለተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን አቶ አዲስ አለማየሁ የካዛና ግሩፕ ሊቀመንበር እና ዶ/ር ገመቹ ዋቅቶላ ዘ አይ ካፒታል ድርጅት መስራች እና የበላይ ሃላፊ የህይወት ተሞክሯቸውን ለተማሪዎች አጋርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር እና አሉሙናይ ዳይሬክተር ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ውጤታማ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ የሚገባቸውን እና ማድረግ የማይገባቸውን ጉዳዮች በመዘርዘር ለተማሪዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡