About AASTU Announcements Applied Sciences Events News News/Events

ማስታወቂያ

ለድህረ ምረቃ (ሁለተኛ  እና ሶስተኛ  ዲግሪ) ትምህርት አመልካቾች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም  የትምህርት ዘመን በአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪያችሁን ለመማር ፍላጎት ያላችሁ የNGAT ፈተና ተፈትናችሁ በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሰረት የፈተና ውጤት 62/125 ማርክ ወይም 80 ፐርሰንታይል ያስመዘገባችሁ አመልካቾች ህዳር 11 – 12 /2016 .   በዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ለምዝገባ ስትመጡ የሚከተሉተን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸሁ በጥብቅ እናሳስባለን ፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

  • የትምህርት ማስረጃ ዲግሪ እና ትራንስክሪፕት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን፤
  • ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፤
  • የወጪ መጋራት የሚመለከታችሁ አመልካቾች ከወጪ መጋራት ነጻ መሆናችሁን እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ በምዝገባ ወቅት ማስላካችሁን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
  • በምዝግባ ወቅት የመመዝገቢያ ክፍያ መክፈላችሁን የሚያረጋግጥ ደረስኝ ያላችሁ (በOnline ላመለከቱ አመልካቾች ብቻ)፤
  • ከግል ከፍተኛ ተቋማት የተመረቃችሁ ተማሪዎች በኢፌዲሪ የት/ት እና ስልጠና ባለስልጣን (ETA) ትክክለኛነቱን የተረጋገጠ (Authenticate የተደረገ ) የት/ት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
  • መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ስፖንሰር የተደረጋችሁ አመልካቾች ኦሪጂናሉን የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችሉ፤

ካሁን በፊት የአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ባወጣው የምዝገባ ማስታዎቂያ   በOnline ማመልከት ያልቻላችሁ ነገር ግን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ በመደበኛው እና በተከታታይ ፕሮግራም መማር የምትፈለጉ የNGAT ፈተና የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971544  የመመዝገቢያ 500 (አምስት መቶ ብር) አዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚል ክፍላችሁ  በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በአካል ተገኝታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስውቃለን። በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ የፕሮግራም ዝርዝር በሚከተሉት ገፆች ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገለጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

  1. ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች የምርምር ስራችሁን ለመስራት ያሰባችሁበትን የምርምር ሃሳብ (concept note/synopsis/draft research proposal) ማቅረቢያ ቀናት ህዳር 13 እና 14/ 2016 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን ፤ 
  2. ለተከታታይ ትምህርት አመልካቾች በየትምህርት ዘርፉ ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር 20 በመሆኑ፤ ከሃያ በታች ለሆኑ አመልካቾች ትምህረት ክፍሉ የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Related posts

Addis Ababa Science and Technology University and IIT ROORKEE Sign Partnership Agreement

aastunew

Under-Graduate CEP Application for 2016 E.C in AASTU

aastunew

Announcing postponement of exam date for all PG applicants

aastunew

Leave a Comment

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy