ለሁሉም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና ተከታታይ መርሃ-ግብሮች መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከሐምሌ 19፤ 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 4 ፤ 2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በይነ መረብ በኩል ምዝገባ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሠረት ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር ከዩኒቨርሲቲው ድህረ ገጽ www.aastu.edu.et እና ኦፊሻል ቴልግራም https://t.me/pir2011 ማግኘት የምትችሉ ሲሆን አመልካቾች ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው መመሪያ መሠረት የሚከተሉትን ነጥቦች አውቃችሁ እንድተገብሩ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
- ሁሉም ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Test (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 21– 25፤ 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ማመልከት የሚገባቸው መሆኑን፣
- የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 – 29፤ 2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፣
- ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲያመለክቱ የመፈተኛ ጣቢያቸውን (ዩኒቨርሲቲ) እና ሌሎች መረጃዎችን በትክክል ተጠንቅቀው መሙላት የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
- ተፈታኞች በGAT የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲሞሉና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚያስፈልገውን ክፍያ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “Addis Ababa University Main Campus” በቴሌ ብር አካውንት 511001 በኩል ብቻ የሚከፍሉ በመሆኑ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት መክፈት እና ዝግጁ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
- ተፈታኞች የፈተና ፕሮግራሞችና ተያያዥ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ- ገጽና ፖርታል www.aau.edu.et እና https://portal.aau.edu.et እንዲሁም ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ማግኘት የምችሉ መሆኑን፣
- በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷችሁ ያለበትን Test Admission Ticket (TAT) ከ (http://portal.aau.edu.et/web/applyForAdmission/TestTaker) አውርደው እና ፕሪንት አድርገው መያዝ የሚጠበቅባቸው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት